በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተከዜ ድልድይ ተጠገነ


ፎቶ ፋይል፦ ተከዜ ድልድል
ፎቶ ፋይል፦ ተከዜ ድልድል

ባለፈው ሰኔ ሃያ ስድስት ፈርሶ የነበረው የተከዜ ድልድይ ተጠግኖ ዛሬ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን መቀሌ የሚገኘው ሪፖርተራችን ሙሉጌታ አጽብሃ ዘግቧል።

ድልድዩ የተጠገነው በኤፈርት ተቋማት እና በህዝቡ ትግግዝ መሆኑን የክልሉ የኮንስትረክሽን እና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ናቸው የተባሉት ወይዘሮ አልማዝ ገብረ ጻድቅ መናገራቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

ፌዴራሉ መንግሥት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት መታገዱን እና ሥልጣኑ የጊዜያዊ አስተዳደሩ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

የድልድዩ መጠገን በክልሉ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን እርዳታ ለማድረስ እገዛ ያደርጋል ቢባልም አሁን ግን አሁን ግን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ለሰው መደበኛ እንቅስቃሴ እና ለጸጥታ አካላት ዝውውር ነው ብለዋል ወይዘሮ አልማዝ።

ለድልድዩ መፍረስ ፌዴራሉ መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀው ህወሓት እና መንግሥቱ ሲወነጃጀሉ ተሰምተዋል።

XS
SM
MD
LG