በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐዲስ አበባ የጤፍ ዋጋ ንረት በልቶ ማደር እንደቸገራቸው ሸማቾች አማረሩ


በዐዲስ አበባ የጤፍ ዋጋ ንረት በልቶ ማደር እንደቸገራቸው ሸማቾች አማረሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:37 0:00

በዐዲስ አበባ የጤፍ ዋጋ ንረት በልቶ ማደር እንደቸገራቸው ሸማቾች አማረሩ

በዐዲስ አበባ ከተማ፣ የጤፍ ዋጋ እየናረ እንደሚገኝ የገለጹ ሸማቾች፣ በልቶ ማደር አዳጋች እየኾነባቸው እንደመጣ አማረሩ።

ከሁለት ወራት በፊት 80 ብር የነበረው የአንድ ኪሎ ነጭ ጤፍ ዋጋ፣ አሁን እስከ 150 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በዐማራ ክልል ጤፍ አምራች በኾኑ አካባቢዎች የተስፋፋውን ግጭት እና አለመረጋጋት ተከትሎ፣ ጤፍን ጨምሮ የምግብ እህሎች በገበያ ላይ በሚፈለገው መጠን እንደማይገኙ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የዐዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ መስፋን አሰፋ በበኩላቸው፣ የእህል ምርቶች፣ የዐማራ ክልልን ጨምሮ ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ወደ ዐዲስ አበባ እየገቡ እንደኾነ ጠቅሰዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩም፣ 1ነጥብ4 ቢሊዮን ብር መድቦ፣ የሰብል ምርት አቅርቦትን ለማሳደግ እየሠራ እንደኾነ አስታውቀዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ጌቴ አንዱዓለም ደግሞ፣ ጤፍን ጨምሮ ለምግብ እህሎች ዋጋ ማሻቀብ፣ የሰላም ዕጦቱ አስተዋፅኦ ቢኖረውም፣ ሌሎች ኢኮኖሚያዊም ምክንያቶች ስለመኖራቸው ያመለክታሉ፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG