በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቲቢ መድሃኒት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ የመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣናት ለአንድ አዲስ ለተሰራ የቲቢ መድሃኒት ጥቃም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጡ። መድኃኒቱ ከሌሎች ሁለት መድሃኒቶች ጋር ሲወስድ ከፍተኛ የሆነ ፍቱንነት እንዳለው ተረጋግጦ ነው ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ የተሰጠው ።

ፕሪቶማኒድ የተባለው መድሃኒት የተሰራው ቲቢ አላያንስ በተባለ ዓላማው ትርፍ ማግኘት ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን ታውቋል።

ፕሪቶማኒድ ከሊሎች ሁለት መድሃኒቶች ጋር የወሰዱ በሌሎች መድሃኒቶች አልበገር ባለ የቲቢ ዓይነት የታመሙ ሰዎች ዘጠና ከመቶውን እንደዳነ ተገልጿል።

የሦስቱ መድሃኒቶች እንድነት ሲወሰዱ በስድስት ወር ጊዜው ህመመታኛው እንደሚያድን መዳሂኒቱንመስደ በጀመረ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሽታውን ወደሌላ ሰው እንዳያይተላፍ የሚያደርግ መሆኑን ነው በመዳሃኒቱ ላይ የተደረገው ጥናት ያመለከተው።

ባሁኑ ጊዜ ለቲቢ ህክምና ጥቅም ላይ የሚውሉት መድሃኒቶች ብዛት ያላቸው ኪኒኖች መዋጥ እና ለበርካታ ወራት በመርፌ የሚሰጥ መድሃኒትም በየቀኑ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ህክምናው እስከሁለት ዓመት ሊወስድም ይችላል። በመሆኑም ብዙ ህመመተኞች በመሰላቸት ወይም ተስፋ በመቁረጥ ህክምናውን ሳይጨርሱ እንደሚተውት ነው ሃኪሞች የሚናገሩት

ቲቢ በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ሰው ይገድላል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG