በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊቷ አቀንቃኝና የዜማ ግጥሞች ጸሀፊ ቴይለር ስዊፍት የግራሚ ተሸላሚ ሆነች


ቴይለር ስዊፍት “ሚድናይትይትስ” በተሰኘው አልበሟ ለ4ኛ ጊዜ የዓመቱ ምርጥ አልበም አሸናፊ ሆናለች፡፡
ቴይለር ስዊፍት “ሚድናይትይትስ” በተሰኘው አልበሟ ለ4ኛ ጊዜ የዓመቱ ምርጥ አልበም አሸናፊ ሆናለች፡፡

ቴይለር ስዊፍት “ሚድናይትይትስ” በተሰኘው አልበሟ ለ4ኛ ጊዜ የዓመቱ ምርጥ አልበም አሸናፊ ሆናለች፡፡ እራት ሽልማቶችን በመውሰድም በዘርፉ የግራሚ ሽልማት ሪከርድ ሰብራለች።

ሽልማቱን ስትቀበል የሙዚቃ አቀናባሪዋን እና ጓደኛዋን ጃክ አንቶኖፍን በማመስገን የጀመረችው ስዊፍት "ይህ በህይወቴ በጣም ደስተኛ የሆንኩበት ጊዜ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ" ብላለች፡፡

ይሁን እንጂ ሙዚቃ ስትፈጥርና ትዕይንቶችን በመድረክ ስትተወንም ይህ ደስታ የሚሰማት መሆኑንም አክላ ተናግራለች። .

ለ13ኛ ጊዜ የግራሚ አሸናፊ የሆነችበት የትናንት እሁድ አጋጣሚ በመጠቀም ቀደም ሲል ምሽቱ ላይ የፊታችን ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ‘Tortured Poets Department’ በሚል ርዕስ አዲስ አልበም እንደምታወጣ አስታውቃለች፡፡

በምሽቱ በተሰጡ ሽልማቶች ማይሌ ሳይረስ “Flowers” ለተሰኘው ሥራዋ የዓመቱን ምርጥ ሪከርድ ስትወስድ፣ ቪክቶሪያ ሞኔት ደግሞ የዓመቱ ምርጥ አዲስ አርቲስት ተብላለች።

ቢሊ ኢሊሽ በበኩሏ የዓመቱን ምርጥ ዘፈን ሽልማት ወደ ቤቷ ይዛ ሄዳለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG