በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአ.አ ነዋሪዎች የታክሲ ዋጋ ጫና እያሳደረብን ነው አሉ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

መንግሥት ከጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ተግባራዊ ያደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ፣ የታክሲ አገልግሎት ዋጋን ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን በማድረጉ በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው መሆኑን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ወ/ት ቤተልሄም ደነቀው እና መምህር ቸርነት ዘውዴ የታክሲዎች እጥረት መኖሩንም ጠቅሰው ወጥትነት የጎደለው የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተናግረዋል።

የአ.አ ነዋሪዎች የታክሲ ዋጋ ጫና እያሳደረብን ነው አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:24 0:00

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ በቅርቡ የተደረገው የታሪፍ ጭማሪ በተለይ ዝቅተኛ የማህበረሰ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገና ወቅታዊውን የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ያማከለ መሆኑን ይናገራሉ።

ኃላፊው አክለውም መንግሥት የትራንስፖርት እጥረትንም ለመግታት ባለፈው ኣመት 100 የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ግዥ ፈጽሟል በቅርቡ ከመንግሥት በተጨማሪ የግል ባለሀብቶችም በዘርፉ ይሳተፉበታል ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG