በቅርቡ ነው ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በመጠነ ሠፊ የሞያ መስኮች የሥልጠና አገልግሎቶች ሰጥተው የተመለሱት። ሥማቸው በእንግሊዝኛ በአጽሕሮት ሲነበብ ተስፋ የሚል ድምጽ ይሰጣል። ለወገናቸው ተሥፋ መስጠት መፈለጋቸውን ለማመላከት የመረጡት መጠሪያ። መቶ ያህል የምሕንድስና ፋኩሊቲዎች፤ ሃያ ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎችና ለመምሕራን ጭምር ልዩ ሥልጠናዎችን ሰጥተዋል።
ከመሥራች አባላቱ ሁለቱን አነጋግረናል። ዶ/ር ያቆብ አስታጥቄ በዩናይትድ ስቴትሱ ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ፕሮግራሞች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኤክትሪክ ምሕንድስና ትምሕርት መምሕር ሲሆኑ አቶ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ በዩናይትድ ስቴትስ የሠራተኞችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ኃላፊ ናቸው። የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ጥናት ማሕበራቸው TASFA የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ተጠሪም ናቸው።
ሙሉውን ውይይት ከዚህ ይከታተሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ