በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ምካፓ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ምካፓ

የቀድሞ የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ምካፓ በሰማኒያ አንድ ዓመታቸው ዛሬ ዓርብ አረፉ።

የቀድሞውን መሪ ዜና ዕረፍት ለህዝቡ በቴሌቭዥን ይፋ ያደረጉት የአሁኑ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ምካፓ ያረፉት ህክምና ላይ በነበሩበት ዳሬሰላም የሚገኝ ሆስፒታል መሆኑን ገልጸዋል።

ቤንጃሚን ምካፓ ታንዛንያን እኤአ ከ1995 እስከ 2005 ከመሩ በኋላ ሥልጣኑን ለተተኪያቸው ለጃካያ ኪክዌቴ አስረክበው መሰናበታቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ በንግግራቸው በታንዛንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት የሰባት ቀን የሃዘን ወቅት ይታሰባሉ፥ የሃገሪቱ ሰንደቅ አላማም ዝቅ ብሎ ይውለበለባል ብለዋል።

ቢንጃሚን ምክፓ ሃገራቸውን በፕሬዚዳንትነት ከመምራታቸው አስቀድመው በማስታወቂያና እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንድሁም በካናዳ አምባሳደርዋ ሆነው አገልግለዋል።

XS
SM
MD
LG