በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛንያ ለጎብኚዎን ልትከፍት ነው


ቀጭኔና አንበሣ፤ ሴሬንጌቲ - ሰሜን ታንዛኒያ - በዓለም ግዙፉ የዱር ሕይወት ጥበቃ ፓርክ /ፎቶ - ፋይል፤ በ2006 ዓ.ም. የተወሰደ/
ቀጭኔና አንበሣ፤ ሴሬንጌቲ - ሰሜን ታንዛኒያ - በዓለም ግዙፉ የዱር ሕይወት ጥበቃ ፓርክ /ፎቶ - ፋይል፤ በ2006 ዓ.ም. የተወሰደ/

ታንዛንያ በዓለምአቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሃል በሯን ለጎብኚዎች ልትከፍት መሆኑ ተሰምቷል።

በዘርፉ የሚሠሩ ብዙዎች በርምጃው መደሰታቸው ቢነገርም በወርርሽኙ ምክንያት ኢንዱስትሪው የተጎዳ መጎዳቱና መንግሥቱም የወርርሽኙን ሥርጭት አድማስ አስመልክቶ ዕውነቱንና በግልፅም ስለማይናገር የውጭ ጎብኚዎች ደፍረው እንዳይሄዱ ሊያደርግ እንደሚችል ሥጋታቸውንም ይናገራሉ።

“ኮሮናቫይረስን ድል አድርገን አስወግደነዋል” ሲሉ ፕሬዚደንት ጆን ማጋፉሊ ባለፈው ግንቦት ቢያውጁም የጤና አዋቂዎች እና የታንዛኒያ ጎረቤቶች ግን “ሃሰት ነው” ሲሉ የፕሬዚዳንቱን መግለጫ አጣጥለዋል።

ከዚያ የፕሬዚዳንቱ መግለጫ ወዲህ ድንበር ኬላ ላይ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ብዙ ታንዛንያዊያን የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ማግኘቷን ኬንያ አስታውቃለች።

ለቫይረሱ የተጋለጠ ስንት ሰው እንዳላት ታንዛንያ ተናግራ አታውቅም።

XS
SM
MD
LG