ለረጅም ጊዜ ሃገሪቱን ሲገዛ የቆየው ፓርቲ የሃገሪቱን የእድገት ደረጃ እንዲያፈጥንና እየጨመረ የሄደውን ከፍተኛ የድህነት መጠን ለመቀነስ የሚቻልበት መንገድ እንዲቀይስ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ለፕረዚዳንትነት እንዲወዳደሩ በማቅረብ በገዢው ፓርቲ ላይ ፋተና ደቅኗል።
“በሀገራችን ሰላም ስላለ ታንዜንያውን በምርጫው ድምጻቸውን እንዲሰጡ እመክራለሁ። በሀገራቸው ታሪክ መስራት የሚችሉበት እድል ይህ ብቻ ነውና። ሰላምና መራጋጋት ስላለ ታሪክ እንድነሰራ እርዱን” ሲሉ ልዋሳ (Lowassa) ጥሪ አቅርበዋል።
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ጂል ክሪግ ትላንት በዳሬሰላም የምርጫ ጣብያዎች ተዘዋውራ ከተመለከተች በኋላ በመዲናይቱ የታየው የምርጫው ሂደት ሰላማዊ ነበር ብላለች።
የምርጫዉን ሂደት እየተከታተለ የሚገኘዉ ሌላዉ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ ቪንሰት መኮሪ (Vincent Makori)ም የምርጫ ካርድ እጥረት ከሚታይባቸዉ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በስተቀር በተለይም በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ያለእንከን በሰላም እንደተካሄደ ገልጿል።
"እንደማንኛዉም የምርጫ ሂደት እዚህም እዚያም ጥቃቅን ችግሮች ነበሩ። በአንዳንድ ቦታዎች የምርጫ ካርድ በጊዜ ባለመድረሱ የድምጽ አሰጣጡ ሂደት ዘግይቶ ነበር። ረጃጅም ሰልፎች ነብሩ። አንዳንዶቹም ወደ ሌላ የምርጫ ጣቢያዎች ለአምሄድ ተገደዋል። አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ የመራጮች ስም ዝርዝር የተመዘገበበት ስነድ ስላልተገኘ እስከሚጣራ ሲጠብቁ ተይቷል። ከነዚህ ዉጪ ግን ምርጫዉ ባብዛኛዉ ሰላማዊ ነበር ለማለት ይቻላል" መኮሪ ሲል ገልጿል።
ከ 140 በላይ የሚሆኑ አለምአቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ሂደቱን ለመከታተል በሀገሪቱ ተግኝተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።