በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ድርድር “ለውጥ እያሳየ ነው” ተባለ


የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ድርድር “ለውጥ እያሳየ ነው” ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:55 0:00

የመንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ድርድር “ለውጥ እያሳየ ነው” ተባለ

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል፣ በታንዛኒያ - ዳሬ ሰላም እየተካሔደ ያለው ድርድር፣ አዎንታዊ ለውጥ እያሳየ እንደኾነ፣ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪ ቡድን በዋና አዛዡ ጃል መሮ ድሪባ እና በምክትላቸው ጃል ገመቹ አቦዬ እንደሚመራ፣ ታጣቂ ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከመንግሥት በኩል፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ ድርድሩን ትላንት እንደተቀላቀሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ይኹን እንጂ፣ ሁለቱም አካላት፣ ድርድሩ ስለሚገኝበት ደረጃ እስከ አሁን የሰጡት መግለጫ የለም፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የሕግ ባለሞያዎችን አስተያየት ተካቶ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG