ዋሺንግተን ዲሲ —
ታንዛንያ ውስጥ ባልታወቀ ሥፍራ ታስረው የነበሩ ሁለት የሲፔጂ አባላት ዛሬ መለቀቃቸው ተገለፀ።
ዋና ጽ/ቤቱ ኒውዮርክ የሆነውና ለጋዜጠኞች መብት መከበር የቆመው ድርጅት ሁለት አባላቱ ካረፉበት ሆቴል በኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ተወስደው ባልታወቀ ስፍራ አንድ ቀን ቆይተው ነው የተለቁት።
ዛሬ ሐሙስ የተለቀቁት ሁለቱ የሲፒጄ ባልደረቦች የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪዋ ማቶኪ ሙሞ እና የአፍሪካ ፕሮግራም ተወኳይዋ አንጄላ ኩንታ ሲሆኑ፣ ሲፒጄ አባላቱ እንዲለቀቁ የተወሰደውን እርምጃ በበጎ ተመልክቶታል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ