በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛኒያ በድርቅ ምክንያት ውሃ በፈረቃ ማደል ጀመረች


የታንዛኒያ የንግድ መዲና ዳሬ ሰላም የመጠጥ ውሃ ምንጭ የሆነው ሩቩ ወንዝ በድርቅ ምክንያት መጠኑ በመቀነሱ ውሃ በራሽን ለማከፋፈል መገደዳቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

እንደ ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ፣ 5.5 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሏት የፓሲፊክ ውቅያኖሷ ከተማ ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ከዚህ በኋላ የሚያገኙት አንድ ቀን እየዘለሉ እንደሆነ በውሃ እና ጽዳት ባለሥልጣን ተነግሯቸዋል።

እንደ አየሩ ሁኔታና የወንዙ ውሃ መጠን መቀነስ ወይም መጨመር ውሃውን የማዳረስ ፕሮግራሙ በየሳምንቱ ሊሻሻል ይችላል ብሏል ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ።

እንደሌሎቹ የምሥራቅ አፍሪካ ጎረቤቶቿ ሁሉ፣ ታንዛኒያም የዝናብ እጥረት ገጥሟታል። የአየር ትንበያ ባለሙያዎች የድርቀት ግዜው ሊራዘም እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው።

ከሩቩ ወንዝ የሚገኘው ውሃ በቀን ከሚያቀርበው 466 ሚሊዮን ሊትር ወደ 300 ሚሊዮን ሊትር መቀነሱና፣ ዳሬ ሰላም በቀን 500 ሚሊዮን ሊትር እንደሚያስፈልጋት ታውቋል።

የታንዛኒያ የሰሜን ጎረቤቶች የሆኑት ኬንያ፣ ሶማሊያና ኢትዮጵያ ዝናቡ ለአራት ወቅቶች ሳይመጣ በመቅረቱ ከአርባ ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ቸነፈር ገጥሟቸዋል።

XS
SM
MD
LG