በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታንዛኒያ ሦስተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አስግቷል


በታንዛኒያ ሦስተኛ ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል አስግቷል።
በታንዛኒያ ሦስተኛ ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል አስግቷል።

በታንዛኒያ ሦስተኛ ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል የታንዛኒያ ባለሥልጣናት እያስጠነቀቁ ነው። ባለሥልጣናቱ ይህን ያሉት ታንዛኒያ ዓለም አቀፉን የኮቪድ-19 ክትባት የሚያከፋፍለው የኮቫክስ አባል ለመሆን ፍላጎቷን ከገለፀች ከቀናት በኋላ ነው። ማስጠንቀቂያውን ተከትሎ መንግሥት ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲወስድና የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀም አስጠንቅቀዋል።

በተለይ ከዩጋንዳ ጋር ድምበር በሚዋሰኑበት አካባቢ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ይህም በሽታው ሀገሪቱን እንደገና ሊያጠቃት ይችላል ሲሉ ቅዳሜ እለት ለጋዜጤኞች መግለጫ የሰጡት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከያ ዳይሬክተር ሊዮናርድ ሱቢ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG