በየመን ሁቲ አማጽያን ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ለበርካታ ሳምንታት ሲቃጠል የቆየው የነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከብ ቀር ባህር ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ብክለት እንዳያስከትል አሳድሮ የነበረውን ሥጋት ማስቀረት መቻሉን አንድ የግል በጸጥታ ጉዳዮች ተቋም ዛሬ አስታወቀ።
አንድ ሚሊየን በርሜል መጠን ያለው ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት ጭኖ በመጓዝ ላይ ሳለ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ጦርነት በመጻረር ዘመቻ የከፈቱት በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች ጥቃት የደረሰበት መርከብ እንዳያስከትል የተፈራውን ብክለት ማስቀረት መቻሉ ተገልጿል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአደጋው ወቅት የፈሰሰው ነዳጅ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1989 በአላስካ ደርሶ ከነበረው ‘የኤክሶን ቫልዴዝ’ አደጋ በአራት እጥፍ ሊከፋ ይችላል’ ሲል ሥጋቱን መግለጹ ይታወሳል።
አደጋውን ለማስቀረት ከአውሮፓ የባህር ኃይል ጋራ የተሰማራው አምብሬ የተባለ ድርጅት አማጽያኑ ባጠመዱት ፈንጂ የተጎዳችውን መርከብ ለማስወገድ፣ እሳቱን ለማጥፋ እና የተረፈውን ነዳጅ ዘይት ለማራገፍ ወራት እንደፈጀም አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም