በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍጋኒስታን ምክር ቤት ምርጫ

በዚህ ወር አፍጋኒስታን ውስጥ የሚካሄደው የምክር ቤት ምርጫ «ከሀቅ የራቀና የውሸት» በመሆኑ፣ ለዚህ ምርጫ መሳካት በሚንቀሳቀሱ ባለሥልጣናትና የደኅንነት ኃይላት ላይ እርምጃ እንዲወስዱ፣ ታሊባን ለተዋጊዎቹ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

በዚህ ወር አፍጋኒስታን ውስጥ የሚካሄደው የምክር ቤት ምርጫ «ከሀቅ የራቀና የውሸት» በመሆኑ፣ ለዚህ ምርጫ መሳካት በሚንቀሳቀሱ ባለሥልጣናትና የደኅንነት ኃይላት ላይ እርምጃ እንዲወስዱ፣ ታሊባን ለተዋጊዎቹ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

አክራሪው ስላማዊ ድርጅት ዛሬ ሰኛ ባወጣው መግለጫ፣ ድምጽ ሰጪዎችም ህኑ ተወዳዳሪዎች ወደ ምርጫ ጣባው እንዳይሄዱ ጥሪ አስተላልፏል። ቡድኑ በዚሁ መግለጫው እንዳስታወቀው፣ «የይስሙላ» ባለው ምርጫ መሳተፍ፣ አፍጋኒስታን ላስቀመጣቸው አሻንጉሊቶች እውቅና መስጠት ይሆናል።

ምንም እንኳ አንዳንድ ፈተናዎች ቢኖሩበትም፣ ለምርጫው መሳካት የሚደረገው ዝግጅት በታቀደው ፕሮግራም መሠረት እየተካሄደ መሆኑን፣ ለታሊባኑ ዛቻ መልስ የሰጡት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ቃል-አቀባይ ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG