ዋሺንግተን ዲሲ —
ምስራቅ አፍጋኒስታን ውስጥ በአንድ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ ሽብርተኞች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ ሃምሳ ሁለት ሰው ሲገደል ከሁለት መቶ የሚበልጡ መቁሰላቸው ተገለጠ።
ፓክቲያ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ጋርዴዝ በሚገኘው የማሰልጠኛ ማዕከል አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ያጨቀበትን መኪና ይዞ ገብቶ ከፈነዳ በኋላ ታጣቂዎች ተከትለው ገብተው ከፖሊሶች ጋር ተታኩሰዋል።
ታሊባን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ