ዋሺንግተን ዲሲ —
የታሊባን ሰርጎ ገብ ቡድን አፍጋኒስታን ውስጥ አንዲት ወረዳ ላይ ጥቃት ከፍቶ ቢያንስ 12 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ። ባለሥልጣናት እንዳመለከቱት፣ የመንግሥቱ የተኩስ አቁም ውል ይፋ ከሆነ በኋላ በተካሄደ ሌላ ጥቃት ወደ 13 ሰዎች የመቁስል አደጋ ደርሶባቸዋል።
ጥቃቱ የተካሄደበት የኮሂስታን ክፍለ ሀገር ቃል አቀባይ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የአፍጋኒስታን ኃይሎች በሲቪሎች ላይ ሊደርስ የሚቸውን አደጋ ለመቀነስ ሲሉ፣ ከክፍለ ሀገሩ ከተማ እያፈገፈጉ መሆናችውን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአፍጋኒስታን ወታደሮች፣ ማዕከላዊ ምሥራቅ ገሃዘኒ ክፍለ ሀገር ውስጥ በምትገነው ሞኩረ ከተማ ውስጥ ከታሊባን ጋር በከባድ ውጊያ መጠመዳቸው ተሰማ።
የአካባቢው የደኅንነት ባለሥልጣናት እንዳረጋገጡት፣ በግጭቱ ስድሥት የሴኩሪቴ አባላት ተገድለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ