ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን ውስጥ ታሊባን እንደገና ጥቃት አደረሰ። በዛሬው ጥቃት ከኢራን ጋር በሚያዋስነው በምዕራባዊው ፋራህ ክፍለ ሃገር ባደረሰው ጥቃት ከአርባ የሚበልጡ የመንግሥቱን ወታደሮች ገድሏል።
የሚበዙት ወታደሮች የተገደሉት ሌሊቱን ታጣቂዎች በፖሊስ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ጥቃት በከፈቱበት ባላ ቡሉክ በሚባል ወረዳ መሆኑ ተገልጿል።
አንድ ከፍተኛ የክፍለ ሃገሩ ፖሊስ ባለሥልጣን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ለበርካታ ሰዓታት በቀጠለው ከባድ ውጊያ የወረዳውን የፖሊስ አዛዥ ጨምሮ ሰላሳ ሁለት የፀጥታ አባላት ሲገደሉ ዘጠኝ ፖሊሶችን ቆስለዋል። ሌሎች አሥራ ሁለት ሃገሮች ደግሞ የደረሱበት ጠፍቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ