በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን አፍጋኒስታን ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ7 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ታሊባን ዛሬ ማለዳ ደቡብ ምሥራቃዊቱ ጋዝኒ ክፍለ ሃገር ውስጥ ባደረሰው ጥቃት አንድ የአውራጃ ዋና አስተዳዳሪና ሰባት ፖሊሶችን ገድሏል።

ታሊባን ዛሬ ማለዳ ደቡብ ምሥራቃዊቱ ጋዝኒ ክፍለ ሃገር ውስጥ ባደረሰው ጥቃት አንድ የአውራጃ ዋና አስተዳዳሪና ሰባት ፖሊሶችን ገድሏል።

ጥቃቱ የተፈፀመው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከግጭቶች ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሲቪሎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከሞቱት ጋር በተመሳሳይ ከፍተኛ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ ነው።

በዛሬው ውጊያ ብዛት ያላቸው በከባድ የታጠቁ የታሊባን ወታደሮች መሳተፋቸውን የክፍለ ሀገሯ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የክፍለ ሃገሩ ፖሊስ አዛዥ ሞሃመድ ዛማን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት ከሆነ የአፍጋኒስታን አጋዥ ኃይሎች በሰዓቱ ደርሰው እርዳታ በመገኘቱ በአሁኑ ወቅት አካባቢው ከታሊባን ተዋጊዎች ፀድቷል።

በመልሶ ማጥቃቱ ላይ ሃያ ሰባት የታሊባን ታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG