በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታሊባን አማፅያን በሰሜን አፍጋኒስታን ወታደሮችን መግደላቸውና መማረካቸው ተገለፀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የታሊባን አማፅያን በሰሜን አፍጋኒስታን የሚገኝ ወታደራዊ ሠፈርን ይዘው በርካት የመንግሥት ወታደሮችን እንደገደሉና እንደማረኩ ታውቋል።

የታሊባን አማፅያን በሰሜን አፍጋኒስታን የሚገኝ ወታደራዊ ሠፈርን ይዘው በርካት የመንግሥት ወታደሮችን እንደገደሉና እንደማረኩ ታውቋል።

ትላንት ፋርያብ ከፍለ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ጎረማች ወረዳ ላይ ያለው ቸናያ ወታደራዊ ሰፈር የተያዘው ከሁለት ቀናት ከባድ ውጊያ በኋላ ነው።

ባለሥልጣኖች እንደሚሉት የሀገሪቱ ብሄራዊ ሠራዊት ሠፈር በታሊባን አማፅያን የተያዘው ወታደሮቹ ደራሽ ኃይልና የአየር ድብደባ ድጋፍ ባለማግኘታቸው፣ መሣርያና ሌሎች አቅርቦቶች ስላለቀባቸው ነው።

በሠፈሩ ከነበሩት 70 ወታደሮች 40ዎቹ ለታሊባን እጃቸውን እንደሰጡ የተቀሩት ደግሞ ተገድለዋል ወይም በአቅራብያው ወዳሉት ተራራዎች ሸሽተዋል ሲሉ የክልሉ ወታደራዊና የመንግሥት ባለሥልጣኖች ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG