በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይዋንና ዩናይትድ ስቴትስ በታይዋን የተመድ ተሳትፎ ተነጋገሩ


 ታይዋን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ራሷን ችላ እንድትወከል የቀረበ ጥያቄ (ፎቶ ፋይል እኤአ 2018)
ታይዋን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ራሷን ችላ እንድትወከል የቀረበ ጥያቄ (ፎቶ ፋይል እኤአ 2018)

ታይዋንና ዩናይትድ ስቴትስ ታይዋን በተባበሩት መንግስታት ውስጥ “ትርጉም ያለው” ተሳትፎ ማድረግ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ተነጋገሩ፡፡

ንግግሩ የተካሄደው፣ ከግማሽ ምዕተ አመት በፊት፣ ታይዋን የቻይና ግዛት መሆኗን ያወጀችበትን እለት አስመልክቶ፣ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዚ ጂፒንግ፣ ንግግር ከሚያሰሙበት ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነው፡፡

ታይዋን በመንግሥታቱ ድርጅት ውስጥ “የቻይና ሪፐብሊክ” በሚል ስም የተወከለችው ፣ እኤአ በ1949፣ የእርስ በርሱ ጦርነት አሸናፊ በሆነቸው ቻይና ስም እንድትወከል፣ የድርጅቱ አባል አገራት፣ እኤአ ጥቅምት 25 1971 ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት ነው፡፡

ቻይና፣ ታይዋን የኔ ግዛት በመሆንዋ ፣ በዓለም አቀፉ መድረክ መወከል ያለባት በኔ አማካይነት ነው ስትል፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የታይፔ መንግሥት ደግሞ፣ የዚያ መብት ባለቤት እኔ ነኝ ይላል፡፡

የዩናትድ ስቴትስ “በዓለም የጤና ድርጅትም ሆነ በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ታይዋን ከምታበርከተው አስተዋጽ አንጻር፣ በተለያዩ የዓለም አቀፉ ጉዳዮች ልትጫወት የምትችለው ድርሻ ያስመስከረች መሆኑን ትገልጻለች፡፡

በመሆኑም “በዓለም አቀፉ ድርጅት ውስጥ ትርጉም ያለው ስፍራ እንዲኖራት ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ቅዳሜ ያወጣው መግለጫም ይህንኑ እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፤

ቻይና፣ ታይዋን የቻይናን ሉዓላዊነት እንድትቀበል የምታደርገውን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጫና አጠንክራለች፡፡

ነጻ አገር መሆንዋን የምትገልጸው ታይዋንም፣ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅና ከቻይና የሚመጣባትን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

XS
SM
MD
LG