በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታይዋን ፕሬዚዳንት የማዕከላዊ አሜሪካ ጉዞ እና የቻይና ማስጠንቀቂያ


የታይዋን ፕሬዚዳንት ታይ ኢንግ ዌን
የታይዋን ፕሬዚዳንት ታይ ኢንግ ዌን

የታይዋን ፕሬዚዳንት ታይ ኢንግ ዌን ከውጭ የሚሰነዘርባት ተጽእኖ ሀገራቸው ከዐለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር እንዳትገናኝ አያደርጋትም ሲሉ ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት ጓቴማላን እና ቤሊዝን ለመጎብኘት ከታይፔይ ከመነሳታቸው አስቀድሞ በሰጡት ቃል ነው፡፡

ፕሬዚዳንቷ ለአስር ቀናት ጉብኝት በሚያደርጉት ጉዞ ኒው ዮርክ ላይ ለአጭር ጊዜ ቆይተው ወደ ጓቴማላ የሚያመሩ ሲሆን ወደሀገራቸው ሲመለሱ ደግሞ በሎስ አንጀለስ በኩል ያልፋሉ፡፡ በዘገባዎች መሠረት በሎስ አንጀለስ ቆይታቸው የአንድ የካሊፎርኒያ ወረዳ ተወካይ ከሆኑት ከዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ኬቭን መካርቲ ጋር ይገናኛሉ፡፡

ታይዋንን ግዛቷ አድርጋ የምትመለከታት ቤጂንግ የአንዲት ቻይናን ፖሊሲ የሚቃረን የታይዋን ሰርጥን ጸጥታም የሚያናጋ የትንኮሳ ተግባር ነው በማለት ፕሬዚዳንቷ ዩናይትድ ስቴትስ መግባታቸውን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡

የቀደሙ የታይዋን ፕሬዚደንቶች ወደሌሎች ሀገሮች ሲጓዙ ዩናይትድ ስቴትስ ቆይታ እያደረጉ እንዳለፉ ያስታወሱት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት በበኩላቸው የአሁኗ ፕሬዚዳንት ታይም እአአ በ2016 እና በ2019 ስድስት ጊዜ ቆይታ አድርገዋል በማለት አሁንም ኒው ዮርክ እና ሎስ አንጀለስ ቆይታ አድርገው እንዲያልፉ መፍቀዳቸው ትክክል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG