በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታይዋን መሪ “ዩናይትድ ስቴትስ ደሴቲቱን እንደምትከላክል አምናለሁ”


ፎቶ ፋይል፦ የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ሊን ዌን
ፎቶ ፋይል፦ የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ሊን ዌን

የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ሊን ዌን “ቻይና ወታደራዊ ጥቃት ብትሰነዝር ዩናይትድ ስቴትስ ደሴቲቱን እንደምትከላከል እምነት አለኝ” ሲሉ ትናትን ረቡዕ ከሴኤንኤን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ተናገሩ፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ ታይዋንን በመካለከል እንደምታግዝ “እምነት አለኝ” ያሉት ሳይ፣ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ዋሽንግተን የታይዋንን ጦር በማሰልጠን ፕሮግራም ለመሳተፍ አሜሪካውያንን ወደዚያው የላከች መሆኑን የፔንታገን ባለሥልጣናትን በመጥቀስ የወጣውን ዘገባ አረጋግጠዋል፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስና ታይዋን በብዙ መልኩ ትብብር አለን” ያሉት የታይዋኗ መሪ፣ ቻይናን ታይዋን በሰላም አብረው መኖር ይችላሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል፡፡

ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

23 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሏት ታይዋን ሯሳን በማስተዳደር ላይ ትገኛለች፡፡

ከቻይና ቋሚ የሆነ ስጋት ቢደነቅባትም ፣ ታይዋን ጨርሳ የማትንበረከክ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቅርቡ በሴኤኔን ቴሌቪዥን ዩናይትድ ስቴትስ ታይዋንን ከየትኛውም የቻይና ጥቃት ትከላከላለች ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ባይደን ያን ሲሉ፣ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ይሁን ሌላ፣ ግልጽ ባለማድረጋቸው፣ ዋይት ሀውስ አባባሉን ከመድገም መቆጠቡ ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG