በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይዋን በመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተጠቃች


ደቡብ ምሥራቅ ታይዋን በመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተጠቃች
ደቡብ ምሥራቅ ታይዋን በመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተጠቃች

ስድስት ነጥብ ስምንት ሪክተር ስኬል የተገመተ የመሬት መንቀጥጥ ደቡብ ምሥራቅ ታይዋንን ከመታ በኋላ የጽዳትና የማገገም ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ የባቡር ተሳቢዎችን ከሃዲዱ ሲያስት፣ የምግብ ሸቀጥ መሸጫ ሱቅ ተደርምሷል።

በአደጋው አንድ ሰው ሲሞት 146 ሌሎች ደግሞ በእሁዱ መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የአየር ትንበያ ቢሮ እንዳለው የእሁዱ መንቀጥቀጥ በተመሳሳይ ቦታ ቅዳሜ ዕለት የተከሰተውን ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ የመጣ ነው።

ከነመኪናቸው ከተሰበረ ድልድይ ላይ ወደ ወንዙ የወደቁ ሦስት ሰዎች ተገኝተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

መንቀጥቀጡ እስከ መዲናዋ ታይፔ ተሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ ህንፃዎች ሲንዘፈዘፉ፣ ከዋናው መንቀጥቀጥ ተከትሎ የሚመጣው መርገብገብ ታይዋንን ሲወዘውዝ ውሏል።

XS
SM
MD
LG