በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የታይዋን ፕሬዝደንት ቻይና ዛቻዋን እንድታቆም ጠየቁ


አዲሱ የታይዋን ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ ደ
አዲሱ የታይዋን ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ ደ

አዲሱ የታይዋን ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ ደ፣ ቻይና ወታደራዊ ማስፈራሪያዋን እንድታቆም ጠይቀዋል።

በበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓታቸው ላይ አዲሱ የታይዋን ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ ደ ባደረጉት ንግግር፣ ቻይና ራስ ገዝ ደሴቷን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት የማይቆም በመሆኑ የሃገሪቱ ዜጎች ለአፍታም እንዳይዘነጉ አሳስበዋል። “ሰላምን በምንሻበት ወቅትም ቢሆን፣ ብዥታ ሊኖረን አይገባም” ብለዋል ላይ ቺንግ ደ።

ቻይና ታይዋንን እንደግዛቷ የምትቆጥራት ሲሆን፣ አስፈላጊ ከሆነም በኃይል ለመቀላቀል ትዝታለች፡፡

በሃገሪቱ መዲና ታይፔ በሚገኘው ፕሬዝደንታዊ ሕንፃ ፊት ለፊት የተካሄደውን ሥነ ስርዓት በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ተከታትለዋል።

“ዊሊያም” በሚል የእንግሊዝ ስማቸውም የሚታወቁት ላይ፣ የሃገሪቱን የቀድሞ ፕሬዝደንት ሥራ በማስቀጠል፣ከቻይና ጋራ ያለውን ግንኙነት ለማረጋጋት እንዲሁም ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን እንደ አሜሪካ ካሉ ሸሪክ ሃገራት በማስገባት የመከላከያ አቅማቸውን ይበልጥ ለማጠናከር አቅደዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG