በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምዷን ቀጥላለች


ሽንዋ የዜና አገልግሎት በለቀቀው ፎቶ አንድ የቻይና አየር ኃይል በታይዋን ደሴት ዙሪያ በረራ ሲያደርግ እና የውጊያ ሥልጠና ልምምዱን ያሳያል እአአ ኦገስት 7/2022
ሽንዋ የዜና አገልግሎት በለቀቀው ፎቶ አንድ የቻይና አየር ኃይል በታይዋን ደሴት ዙሪያ በረራ ሲያደርግ እና የውጊያ ሥልጠና ልምምዱን ያሳያል እአአ ኦገስት 7/2022

ቻይና በታይዋን ባህርና ሰማይ ዙሪያ የምታደርገው ወታደራዊ ልምምድ ዛሬ ሰኞም ቀጥሎ መዋሉን የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የቻይና ህዝብ ነጻ አውጭ ሰራዊት የምስራቅ ወታደራዊ ትርኢት አዛዥ፣ ዌቢቦ በተሰኘው ማህበራዊ መድረክ ባወጡት መግለጫ፣ የጸረ ባህር ሰርጓጅ ጥቃት እና የባህር ላይ ወረራ ልምምዶች እደሚካሄዱ አስታውቀዋል፡፡

እስከ ትናንት እሁድ ድረስ ለአራት ቀናት ይቆያል የተባለው ጠንካራው ወታደራዊ ልምምድ ዛሬም መቀጠሉ የተመለከተ ሲሆን ቃል አቀባዩ እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችል አላመለከቱም፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ አፈጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ ወዲህ ቻይና ያልተለመዱ የባህርና የአየር ኃይል ልምምዶችን በታይዋን ዙሪያ ስታካሂድ መቆየቷ ተገልጿል፡፡

የቻይና መከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ው ኪያን በድረገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “አሁን በታይዋን የባህር መተላለፊያ ያለው ውጥረት በጠቅላላ የተፈጠረው በዩናይትድ ስቴትስ፣ በራሷ አነሳሽነት በመሆኑ በዩናይትድ ስቴት በኩል ያለው ወገን ሙሉ ኃላፊነቱንና የሚያስከተለውን አደገኛ መዘዝ መሽከም አለበት” ብለዋል፡፡

ልምምዱ የታይዋን አየር ክልል ያቋረጠውን የባለስቲክ ሚሳዬል ጨምሮ፣ የጦር መርከቦች፣ ተዋጊ ጀቶች፣ ድሮናችና የመሳሰሉት የጦር መሳሪያዎች በደሴቲቱ አካባቢ በተደረገው ልምምድ መሳተፋቸው ተነገሯል፡፡

ትናንት እሁድ ከቻይናና ታይዋን የተውጣጡ ወደ 10 የሚጠጉ የጦር መርከቦች፣ ከተፈቀደው መደበኛው የባህር ክልል መስመር ውጭ፣ በጣም በተቀራረበ ርቀት ሲተላለፉ እንደነበር፣ ለጉዳዩና ለደህንነት እቅድ ቅርበት ያላቸው ሰው ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG