በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጉዳቱ መክሊቱን ያበዛው ባለአንድ እግሩ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋና አሠልጣኝ


በጉዳቱ መክሊቱን ያበዛው ባለአንድ እግሩ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋና አሠልጣኝ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:32 0:00

በጉዳቱ መክሊቱን ያበዛው ባለአንድ እግሩ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋና አሠልጣኝ

የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶችን፣ ከራሱ የሕይወት ገጠመኝ እየተነሣ፣ በሥነ ምግባር እየኮተኮተና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብቁ እያደረገ የሚገኘውን፣ ባለአንድ እግሩ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋና አሠልጣኝ ወይም በዘርፉ የማዕርግ አጠራር ሳቦም ከማል ቃሲምን፣ የዛሬ ጋቢና ቪኦኤ ዝግጅታችን እንግዳ አድርገነዋል፡፡

በአፍሪቃ ድንቃድንቅ መዝገብ ስሙ የሰፈረው ብቸኛው ባለአንድ እግሩ አሠልጣኝ በሚሰጠው የቴኳንዶ ሥልጠና ደስተኛ ቢኾንም፣ በብዙ የሕይወት ፈተናዎች ውስጥ እንዳለፈና እያለፈ እንደሚገኝም ይናገራል፡፡

ሳቦም ከማልን ለአካል ጉዳት የዳረገው አጋጣሚ የተፈጠረው፣ ገና የስድስት ዓመት ሕፃን እያለ በ1985 ዓ.ም. ነበር፡፡ የ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥን ያማጣው ጦርነት ቅሪት በኾነና በወረታ ከተማ በተተወ ታንክ ላይ የተቀመጠ ብረትን ሲቀጥቅጥ የተከሠተው ፍንዳታ ባደረሰበት ጉዳት አንድ እግሩን አጥቷል፡፡

አደጋው፣ ሳቦም ከማልን ለዕድሜ ልክ የአካል ጉዳት ቢዳርገውም፣ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ በገነባው ጠንካራ ሰብእና ስኬትን ለመጎናጸፍ በቅቷል፡፡ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ለሚገኙ ሠልጣኝ አዳጊዎች እና አፍላ ወጣቶች ከገጠመው እየተነሣ አበክሮ ይመክራቸዋል፡፡ ዕለታዊ የሥልጠና መርሐ ግብሩ መዝጊያ፣ ልጆች አንዳችም የወደቀ ብረት እንዳይቀጠቅጡ የሚያስጠነቅቅ ነው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG