በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከሜክሲኮ፣ ካናዳ እና ቻይና በሚመጡ ምርቶች ላይ "በአፋጣኝ ቀረጥ እጥላለሁ" አሉ


የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሦስቱ የሀገራቸው ዋነኛ የንግድ ሸሪኮች ከሜክሲኮ ካናዳና ቻይና በሚገቡ ምርቶች እና ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ እንደሚያደርጉ አመለከቱ።

የተባለው የቀረጥ ጭማሪ ከሀገራቱ ጋራ “የንግድ ጦርነት ይቀሰቅሳል፣አሜሪካውያን ሸማቾች ላይም የሸቀጥ ዋጋ እንዲንር ያደርጋል” ተብሏል።

ትረምፕ እቅዳቸውንን አስመልክቶ “ትሩዝ ሶሻል” በተባለው የማኅበራዊ መልዕክቶች መላላኪያቸው ላይ በተከታታይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የፊታችን ጥር አጋማሽ ላይ ዋይት ሃውስ እንደገቡ በመጀመሪያዋ ቀን "ከሜክሲኮ እና ከካናዳ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገቡ ሁሉም ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ጭማሪ የሚያስከፍሉ ለውጦች የሚያደርጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም “ጅላጅል” ያሉትን ‘ልቅ የተተወ’ ድንበር አያያዝ የሚመለከቱ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች በሙሉ ወዲያውኑ እፈርማለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።

"የቀረጥ ጭማሪው በተለይም ፈንቲኔል በመባል የሚታወቀውን ጨምሮ ወደ አሜሪካ የሚገቡ አደገኛ እጾች እና መድሃኒቶች፤ እንዲሁም ‘ህገ ወጥ ፍልሰተኞች ወረራ’ ያሉትን እስኪያስቆሙ ድረስ ጸንቶ እንደሚቆይም ገልጸዋል። ሜክሲኮ እና ካናዳ “ይህን ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የቆየ ችግር በቀላሉ የመቅረፍ ችሎታ አላቸው” ብለዋል ትረምፕ።

ቻይናን አስመልክተውም “ከፍተኛ መጠን ያላቸው አደገኛ መድኃኒቶች በተለይም ፌንቲኔል ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገባበት መንገድ ላይ” አላት ስላሉት ሚና ቅሬታ አሰምተዋል ።

"እናም ያን ማስቆም እስከምትችል ድረስ ቻይና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገቡ ምርቶቿ በሙሉ ላይ በአሁኑ ወቅት ተጥሎባት ከሚገኘው በተጨማሪ የ10 በመቶ ተጨማሪ ቀረጥ እናስከፍላታለን" ብለዋል።

የትረምፕን አስተያየት ተከትሎም ቻይና በሰጠችው ምላሽ “በንግድ ወይም በቀረጥ ዙሪያ በሚደረግ ፍልሚያ" ማንም አያሸንፍም"ብላለች።

"የቻይና እና የዩናይትድ ስቴትስ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር በተፈጥሮው ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፤ ብላ ቤጂንግ ታምናለች" ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሊዩ ፔንዩ ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በቀደመው የትረምፕ አስተዳደር የንግድ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። በውላቸውም መሰረት ስምምነቱ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2026 ዓም ይገመገማል።

ስምምነቱ ከብሔራዊ ደህንነት ጋር የተዛመዱ የንግድ ልውውጦች ላይ የቀረጥ ጫናዎቹ ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው ይፈቅ

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG