በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶርያውያን አማፅያንና ቤተሰቦቻቸው ከምስራቃዊ ጎታ አካባቢ ይወጣሉ

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሶርያውያን አማፅያንና ቤተሰቦቻቸው ከሶርያ አጋር ሩስያ ጋር በተደረገው ሥምምነት መሰረት ዛሬ ከተከበበው ምስራቃዊ ጎታ አካባቢ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሶርያውያን አማፅያንና ቤተሰቦቻቸው ከሶርያ አጋር ሩስያ ጋር በተደረገው ሥምምነት መሰረት ዛሬ ከተከበበው ምስራቃዊ ጎታ አካባቢ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አንድ የአውቶብሶች ቡድን ሰዎቹን ከሐራሳታ በሰሜን ሶርያ በተቃዋሚ አማፅያን ወደ ተያዘው ዒድሊብ ያጓጉዛል።

ከዚህ ቀደምም አማጽያኑ የመንግሥት ኃይሎች ጥቃት ሲበረታባቸው ወደ ሌላ የአማፅያን ክልል ለመሄድ እንዲህ አይነቱን ሥምምነት ሲጠቀሙ ቆይተዋል።

የዛሬው ሥምምነት ከሶርያ መንግሥት ጋር የተደረገ የእስረኞች ልውውጥንም ያካትታል።

የሶርያ መንግሥት በሩስያ እየተረዳ አካባቢዎን መልሶ ለመቆጣጠር ከአንድ ወር በፊት በከፈተው ጥቃት ምሥራቅ ጎታን በብዙ ቦታዎች ከፋፍሏል፡፡ 1ሺሕ 5መቶ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ አልቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG