ዋሺንግተን ዲሲ —
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመራ የሶሪያ አዲስ የሰላም ድርድር በቀጣዩ ሳምንት ሊጀመር ዕቅድ ተይዟል።
ባሁኑ ወቅት ዛሬ ረቡዕ ተቃዋሚ መሪዎቹ ጠንከር ያለ የአንድነት አቋም ይዘው ለመቅረብ ሳውዲ አረብያ ውስጥ ተሰባስበው እየመከሩ ናቸው።
በሶሪያው ግጭት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያለ ተሰሚነት ያላቸው በርካታ ሌሎች ሀገሮች ደግሞ ሩስያ ውስጥ የራሳቸውን ምክክር ይዘዋል።
እኤአ በ2011 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድን የሚቃወሙት ሽምቅ ተዋጊዎች በተበታተነ ሃይል ከተሰለፉ ቆይተዋል። በመሆኑም በአንድ የጋራ ድርጅት የመሰባሰብ ሙከራቸው በተለያዩ አንጃዎች አለመግባባት ምክንያት ሲጓተት ቆይቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቱ ልዩ የሶሪያ ልዑክ ስቴፋን ዲ ሚስቱራ ዛሬ ሪያድ ውስጥ በድርድሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በሚቀጥለው ሳምንት ጄኔቫ ውስጥ በሚካሄደው ድርድር ላይ ጠንካራና የሆነ የእንድነት አቋም የያዘ የተቃዋሚዎች ልዑካን ቡድን ሊገኝ ይገባል ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ