በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶርያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን እስራኤልን ከሰሰ


ሁለት የእስራኤል ሚሳይሎች በደማስቆ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ አጠገብ ያሉ ዒላማዎችን መተዋል ሲል የሶርያ መንግሥት ሚድያ ዛሬ ከሷል።

ሁለት የእስራኤል ሚሳይሎች በደማስቆ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ አጠገብ ያሉ ዒላማዎችን መተዋል ሲል የሶርያ መንግሥት ሚድያ ዛሬ ከሷል። 'ሳና' የተባለው የሶርያ የዜና አገልግሎት ስላደረሰው ጉዳት አልተናገረም። ብሪታንያ ሆኖ የሶርያን ጉዳይ የሚከታተለው የሰብዓዊ መብት ቡድን ግን ሚሳይሎቹ የመንግሥት ደጋፊ ሚሊሻዎች የመሳርያ መጋዘን ነው ተብሎ የሚጠረጠር ቦታን መተዋል ይላል።

እስራኤል በሶርያው ግጭት ወቅት በተደጋጋሚ የአየር ድብደባ ስታካሄድ ቆይታለች። ሊባኖስ ላለው በኢራን የሚደገፍ ህዝብ አላህ የሚላክ መሳርያ ለማቆምና ኢራን በሶርያ ላይ ህላዌ እንዳይኖራት ለመከላከል የምትወስደው ዕርምጃ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG