የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ዛሬ ዓርብ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፣ መሪውን አቡ ዮሱፍን ጨምሮ ሁለት የአይሲስ አባላት ሶሪያ ውስጥ በተፈጸመ አየር ጥቃት ተገድለዋል።
የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ሐሙስ መሆኑን ያስታወቅቁት የዕዙ መሪ ጀኔራል ማይክል ኩሪላ፣ የአይሲስ መሪዎችና ዓባላት ዒላማ መደረጋቸው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
አሜሪካ አይሲስ በሶሪያ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ሊያንሰራራ ይችልላ የሚል ሥጋት እንዳላት ማስታወቋን የጠቆመው የሮይትረስ ዘገባ፣ በሀገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ በቱርክ በሚደገፉት አማጺያን እና ከአሜሪካ ጋራ ባበሩት የኩርድ ሚሊሺያዎች መካከል ግጭት እንዳይኖር እንደምትሻ አመልክቷል።
ምዕራባውያን መንግስታት ‘ሃያት ታህሪር አል-ሻም’ ወይም በምጻሩ ‘ኤች ቲ ኤስ’ በመባል የሚታወቀውንና በሶሪያ የቀድሞ አል ቃይዳ ቅርንጫፍ ቡድን ጋራ ንግግር ለመክፈት እንደሚሹና በሽብርተኝነት መፈረጁን ለማንሳት ክርክር መጀመራቸውንም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም