በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶሪያ አይ ኤስ በሺዓ ሙስሊም መስጂድ ላይ ያቀደውን ጥቃት አከሸፈች


ሳይዳ ዘይነብ ደማስቆ እ.ኤ.አ ሰኔ 26/ 2016
ሳይዳ ዘይነብ ደማስቆ እ.ኤ.አ ሰኔ 26/ 2016

የአዲሱ የሶሪያ መንግስት የድህንነት ሃላፊዎች እራሱን እስላማዊ መንግስት እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን በደማስቆ ሳይዳ ዘይነብ አካባቢ በሺዓ ሙስሊሞች የአምልኮ ስፍራ ላይ ሊያደርስ የነበረውን የቦምብ ጥቃት ማክሸፋቸውን እንዳስታወቁ የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የሀገሪቱ መንግስት የሚተዳደረው ሳና መገናኛ ብዙሃን በሀገሪቱ ደህንነት ውስጥ የሚያገለግሉ ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ ጥቃቱን ሊፈጽሙ የነበሩ የአይ ኤስ አባላት መታሰራቸውን ዘግቧል።

ባለሥልጣኑ የስለላ አገልግሎቱ “የሶሪያን ሕዝብ በሁሉም አቅጣጫ ለማጥቃት የሚደረጉ ሙከራዎችን ሁሉ ለማምከን በሙሉ አቅሙን እየተጠቀመ ነው” ማለታቸው ተዘግቧል።

የሱኒ እስልምና ጽንፈኛ የሆነው አይ ኤስ ቡድን የሺዓ ሙስሊሞችን እና ሳይዳ ዘይናብን እንደመናፍቅ የሚቆጥር ሲሆን፤ ስፍራው ከዚህ ቀደምም ለጥቃቶች የተጋለጠ ነው።

እ.ኤ.አ. በ 2023 በሺዓ ሀይማኖት እንደ ቅዱስ ቀን ከሚታሰበው አሹራ በዓል ዋዜማ በሰይዳ ዘይናብ ውስጥ ፈንጂዎችን የያዘ ሞተር ሳይክል ፈንድቶ በትንሹ ስድስት ሰዎችን ሞተው በደርዘን የሚቆጠሩ መቁሰላቸው ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG