በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ሶሪያን ደበደበች


ሶሪያ አሌፖ
ሶሪያ አሌፖ

እስራኤል ከበድ ያለ የተባለ ድብደባ በሰሜን ሶሪያ አሌፖ ላይ ዛሬ ዓርብ በማለዳ ፈጽማለች፡፡ ድብደባው የኢራን ቅጥረኛ በሚባሉ ኃይሎች ላይ ከጋዛው ጦርነት ጎን ለጎን የጀመረችው ዘመቻ አካል እንደሆነ ታውቋል።

በኢራን ይደገፋል የሚባለው ሐማስ ባለፈው መስከረም ጥቃት ከፈፀመ ወዲህ፣ እስራኤል በሌባኖስ ሄዝቦላ እና በኢራን አብዮታዊ ዘብ ላይ የአየር ድብደባዋን አጠናክራ ቀጥላለች። የጦር አብራሪዎቿም ወደ ሌባኖስ ዘልቆ በመግባት ድብደባ ለማድረግ በልምምድ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

አሌፖን እና መዲናዋን ደማስቆ ጨምሮ፣ ኢራንና አጋሮቿ በመላ ሶሪያ ወታደራዊ ይዞታ አላቸው። እስራኤል በተደጋጋሚ በሁለቱም ከተሞች የሚገኙ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያዎችን ደብድባለች፡፡ ይህም ከኢራን የሚገባውን መሣሪያ ለማስቆም እንደሆነ ይነገራል።

ከሐማስ ጥቃት ወዲህ የሚፈፀሙ ድብደባዎች የሰው ሕይወት እየቀጠፉ በመምጣታቸው፣ ኢራን አንዳንድ ወታደራዊ አዛዦቿን ከሶሪያ እንድታስወጣ አስገድዷል። የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ በዛሬው ሌሊት ድብደባ በአሌፖ በስተደቡብ በርካታ ሲቪሎች እና የጦር ዓባላት ተገድለዋል። የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ድብደባውን በተመለከተ አስተያየት ያልሰጠ ሲሆን፣ የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ናሰር ካናኒ ግን፣ በአካባቢው ያለውን ጦርነት ለማስፋት በተስፋ መቁረጥ የተፈፀመ ጥቃት ነው ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG