ዋሺንግተን ዲሲ —
በዛሬው ዕለት ከተማዋን የሚለቁ ነዋሪዎችን በሚያጓጓዙ ኮንቮይ አቅራቢያ ፍንዳታ ተሰምቷል።
ከአሳድ ሃይሎች ጋር የደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት የጣሱት ሽምቅ ተዋጊዎቹ ናቸው ሲሉ የመንግሥቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የተቋረጠው ነዋሪዎችን የማስወጣቱ ሂደት መቼ ሊቀጥል እንደሚችልም ግልፅ የሆነ ነገር የለም።
ከምሥራቅ አሊፖ ከተማ የሚወጡ የቪድዮ ቅጅዎች መንግሥት በተቆጣጠረው አንድ አካባቢ የአምቡላንስ መኪኖችና አውቶብሶች ሲደርሱ ያሳያሉ፡፡
በዚያም በበዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ሌላ አማፂያኑ ወደሚቆጣጠሩዋቸው ግዛት ለመሄድ እየተጠባበቁ ነው፡፡
ዘላቲካ ሆክ ያጠናቀረችው ዘገባ አለ፤ ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡