በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሶሪያ የርስ በርስ ጦርነትና ቀውስ የፖለቲካ መፍትኄ ዓለምአቀፍ ጉባዔ በብራስልስ


ፎቶ ፉይል
ፎቶ ፉይል

ለሶሪያ የርስ በርስ ጦርነትና ቀውስ የፖለቲካ መፍትኄ ለማስገኘት የታሰበ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ዛሬ ቤልጅግ ዋና ከተማ ብራስልስ ውስጥ እንደገና ተጀምሯል።

ለሶሪያ የርስ በርስ ጦርነትና ቀውስ የፖለቲካ መፍትኄ ለማስገኘት የታሰበ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ዛሬ ቤልጅግ ዋና ከተማ ብራስልስ ውስጥ እንደገና ተጀምሯል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአውሮፓ ኅብረት ጣምራ ሊቀመንበርነት ይመራል በተባለው በዚህ የሁለት ቀናት ጉባዔ ላይ ከሰማንያ አምስት ሃገሮች የተጋበዙ ሚኒስትሮችና የመንግሥታት ተጠሪዎች እየተሣተፉ ናቸው።

ከጉባዔው ዓላማዎች መካከል ለሶሪያዊያን ሰብዓዊ እርዳታ ማሰባሰብና በመንግሥታቱ ድርጅት ለሚመራው የጄኔቫ የሰላም ሂደት ድጋፍ ማስገኘት መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ በሩሲያ የሚታገዙት የሶሪያ የመንግሥት ኃይሎች ወታደራዊ ድል ለማወጅ እየገሠገሱ በመሆናቸው ከብራስልስ የሚያጠረቃ የዲፕሎማሲ ስኬት ዜና ይጨበጣል ተብሎ እንደማይጠበቅ እየተሰማ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG