በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስዊዘርላንድ የቀድሞ የጋምቢያ ሚኒስትርን ፍ/ቤት ልታቆም ነው


የቀድሞው የጋምቢያ መሪ ያህያ ጃሜህ ባንጁል አውሮፕላን ጣቢያ፤ ጋምቢያ እአአ ጥር 17/2017
የቀድሞው የጋምቢያ መሪ ያህያ ጃሜህ ባንጁል አውሮፕላን ጣቢያ፤ ጋምቢያ እአአ ጥር 17/2017

የስዊዘርላንድ ዐቃቤ ሕጎች፣ የቀድሞው የጋምቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትርን፣ በሰብአዊነት ላይ ፈጽመውታል ባሉት ወንጀል እንደከሠሧቸው፣ ዛሬ አስታውቀዋል፡፡

ክሡ፥ የአገሪቱን የረጅም ጊዜ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ይቃወሙ በነበሩት ላይ፣ ሚኒስትሩ ኡስማን ሶንኮ፣ ለዓመታት ፈጽመውታል በተባሉት የመብቶች ጥሰት ምክንያት የቀረበባቸው እንደሆነ ታውቋል።

ኡስማን ሶንኮ፣ እአአ ከ2006 እስከ 2016፣ በቀድሞው ፕሬዚዳንት በያህያ ጃሜህ አገዛዝ ወቅት፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ ከሰባት ዓመታት በፊት፣ በስዊዘርላንድ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቁም፣ በዓመቱ ወደ ወህኒ ወርደዋል።

የአገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳለው፣ ትላንት ለፌዴራል ወንጀል ችሎት የቀረበው ክሥ፣ ለ16 ዓመታት ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን የሚመለከት ነው።

የቀድሞው የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሶንኮ፣ በጋምቢያ ተቃዋሚዎች ላይ በደረሰው ጥቃት በመሳተፍ፣ ጥቃቱን በመደገፍ እና ጥቃቱን ባለመከላከል የሚሉ ክሦች ቀርበውባቸዋል።

XS
SM
MD
LG