በስዊድን አንድ ግለሰብ በጎልማሶች ትምህርት ቤት ውስጥ በከፈተው ተኩስ ግለሰቡን ጨምሮ 11 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ሌሎች አምስት ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ተጎድተዋል ተብሏል።
ፖሊስ ግለሰቡ ድርጊቱን ለብቻው መፈጸሙን ገልጾ፣ የትምህርት ቤቱ ተማሪ ይሆን እንደሁ ወይም ምን እንዳነሳሳው አላሳወቅም።
የጅምላ ግድያው በስዊድን ታሪክ የከፋው እንደሆነ ተነግሯል።
ግድያው የተፈጸመው ከስቶክሆልም ወጣ ብሎ በሚገኝና ለጎልማሶች የአንደኛና የሁለተኛ ደርጃ ትምህርት እንዲሁም ለስደተኞችና ለሌሎችም የቋንቋና የሙያ ትምህርት በሚስጥበት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።
ስዊድን ውስጥ በትምህርት ተቋማት በመሣሪያ የሚፈጸም ግድያ እምብዛም አይስተዋልም።
መድረክ / ፎረም