በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ አንድ ታጣቂ ት/ቤት ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 13 ሰዎች ሞቱ


ሩሲያ፣ ኢዝሄቭስክ ከተማ የሚገኘው ት/ቤት ጉዳቱ ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ፖሊስ አካባቢውን ሲጠባበቅ
ሩሲያ፣ ኢዝሄቭስክ ከተማ የሚገኘው ት/ቤት ጉዳቱ ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ፖሊስ አካባቢውን ሲጠባበቅ

ሩሲያ ውስጥ ከሞስኮ 970 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ኢዝሄቭስክ ከተማ በሚገኝ ትምህር ቤት ውስጥ አንድ ታጣቂ ዛሬ ሰኞ ባደረሰው ጥቃት ሰባት ህጻናትን ጨምሮ 13 ሰዎች በመግደል ከ20 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ማቁሰሉ ተነገረ፡፡

በለበሰው ካኒቴራ ላይ ስዋስቲካ የተሰኘውን የናዚ አርማ መልበሱ የተገለጸው አጥቂ ጉዳቱን ካደረሰ በኋላ ራሱን ማጥፋቱንና ጥቃቱን ያደረሰበት ምክንያት አለመገለጹን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡

ትላልቅ ወንጀሎችን የሚያየው የሩሲያ መርማሪዎች ኮሚቴ አጥቂው ከአይንና አፉ በስተቀር ፊቱን የሚሸፍን ጭምብል አጥልቆ እንደነበር አስታውቋል፡፡ የመማሪያ ክፍል ውስጥ የነበሩ ቁሳቁሶችን በመበታተን ከወለሉ የተዘረረው አጥቂ ጥቁር በጥቁር ልብስ ያደረገና ደረቱ ላይ ዙሪያውን የተከበበ በቀይ የተሳለ የስዋስቲካ አርማ ማድረጉ በተለቀቀው የቪዲዮ ምስል ተመልክቷል።

ጥቃቱ ከደረሰባቸው መካከል 6 መምህራንና የጥበቃ ሠራተኞ የሚገኙበት ሲሆን 14 ህፃናትን ጨምሮ ከ21 ሰዎች በላይ መቁሰላቸውን መርማሪው ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ታጣቂው ሁለት ሽጉጦችን ከበርካታ ጥይቶች ጋር ታጥቆ እንደነበር መርማሪዎች መናገራቸውን የታስ ዜና ማሰራጫን የጠቀሰው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሩሲያ በትምህርት ቤቶች ላይ የሚፈጸሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ማስተናገዷን ዘገባው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG