በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

United States በኤርትራ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች ብለዋል ሱዛን ራይስ


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ የ United States ተወካይ ሱዛን ራይስ ኤርትራ በአከባቢዋ በምታሳየው ባህሪ ምክንያት አለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣልባት የሚደረገውን ጥረት United States ትደግፋለች ብለዋል። ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ውይይትና ክርክር የሚደረግበት ቢሆንም United States ወቅቱ ነው ብላ ታምናለች ይላሉ ሱዛን ራይስ።

“ለዐል ሸባብ የምትሰጠው ድጋፍና የጎረቤት ሀገሮችን መረጋጋት ለማደፍረስ የምታደርገው ድጋፍ በልዩ የጸጥታው ምክር ቤት ኮሚቴ ዘገባ በሰፊውና አሳማኝ በሆነ መንገድ ቀርቧል። ባለፈው ወር በተደረገው ስብሰባም ከሞላ ጎደል ሁሉም የኤርትራ ጎረቤት ሃገሮች አሳሳቢ የሆነ የመረጋጋት ማደፍረስ ተግባር እንደሚገጥማቸው ገልጸዋል።” ሲሉ ሱዛን ሪይስ አስገንዝበዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ አማባሳደር አርአያ ደስታ በበኩላቸው “አንዲት ትንሽና አዲስ ሀገር በነዚህ ሃገራት ሁሉ እንዴት ችግር ልትፈጥር እንደምትችልና ምን ያህል ልዕለ-ሃያል እንደሆነች ሊገባኝ አይችልም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

XS
SM
MD
LG