በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች ከተገደሉበት ጥቃት ያመለጡ ግድያው እንዴት እንደተፈጸመ ገለጹ


ከጥቂት ቀናት በፊት ጥቃቱ የደረሰው ነዋሪዎቹ እአአ ባለፈው 2021 የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት ማጣጣም እየጀመሩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ተመልክቷል።

ባንካስ በተባለው የሀገሪቱ አካባቢ ለሁለት ቀናት በዘለቀው የታጣቂዎች ጥቃት ቢያንስ 132 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የሀገሪቱ መንግሥት ጥቃቱን የፈጸሙት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ጽንፈኛ እስላማዊ አማጽያን ናቸው ሲል ወንጅሏል።

ይሄኛው ጥቃት ከሁለት ዓመታት በፊት የፕሬዚዳንት ቡባካር ኬይታን መንግሥት ያመጹ ወታደሮች ከገለበጡት ወዲህ ብዛት ያለው ሰው የተገደለበት መሆኑን ተንታኞች አመልክተዋል።

የጽንፈኛ ታጣቂዎች ሁከት ከሰሜናዊው የሀገሪቱ አካባቢ ወደማዕከላዊ ክፍለ ግዛቷ በመስፋፋት ላይ መሆኑንም ተንታኞቹ መግለጻቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG