በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመስከረም አንዱ የአሸባሪ ጥቃት ሲታወስ


ፎቶ ፋይል፦(ትዊን ታወርስ)
ፎቶ ፋይል፦(ትዊን ታወርስ)

እአአ መስከረም አስራ አንድ 2001 በኒው ዮርክ የዓለም የንግድ ማዕከል መንታ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች(ትዊን ታወርስ)፥ አርሊንግተን ቨርጂኒያ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ህንጻ ፔንታገን እና በፔንሲልቬንያ ሻንክስቪል በጠቅላላው ቁጥራቸው ወደሶስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ጠፍቷል።

የዚያ ዓመት የአዲስ ዓመት በዓል እንቁጥጣሸ ዕለት በኢትዮጵያውያን ቤተሰቦችም ላይ እጅግ መሪር ሃዘን የወደቀበት ቀን ነበር።

ተግተው ተምረው ለትልቅ የሙያ ስኬት የበቁ ገና በሰላሳ ዐመት እድሜ ውስጥ የነበሩ ለብዙ ስኬት ይጠበቁ የነበሩ ወጣቶች ህይወት ተቀጥፏል።

ወይዘሮ ፈለቁ ክፍሉ በኒው ዮርክ የዓለም የንግድ ማዕከል አንደኛው ህንጻ ላይ ለሞርጋን ስታንሊ ኩባኒያ ትሰራ ነበር። ያን ዕለትም ጠዋት ቀደም ብላ ነበር ስራ የገባችው። ለወትሮው የእንቁጣጣሽ ቀን አልገባም ነበር፥ የገባሁት ዕረፍት ላይ ከርሜ እንደተመለስኩ ስለነበር ቀኑ ተምታቶብኝ ነው ብላለች። ከስድስተኛው ፎቅ ከባልደረቦቿ ጋር ከወጣችበት ግዜ ጀምራ ያሳለፈችውን ጭንቀት ይበልጡንም ያየችውን ዘግናኝ ሁናቴ ወደኋላ መለስ ብላ በትካዜ ታስታውሳለች።

የመስከረም አንድ ጥቃት ህይወቷን እንዴት እንደቀየረው ታወጋናለች። በየዓመቱ በዚህ ቀን ምን እንደሚሰማት በመግለጽ ትጀምራለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የመስከረም አንዱ የአሸባሪ ጥቃት ሲታወስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:36 0:00


XS
SM
MD
LG