በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲክቶክ በአሜሪካ እንዲታገድ የፌዴራል ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ አጸና


ቲክቶክ
ቲክቶክ

ቲክቶክ እስከ መጪው ዕሁድ ድረስ ከቻይና ኩባንያ ባለቤትነት ወጥቶ ለሌላ አካል ካልተሸጠ በአሜሪካ እንዲታገድ የፌዴራል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በሙሉ ድምጽ አጽንቶታል።

ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ዛሬ በሰጠው ውሳኔ፣ ቲክቶክ ከቻይና ጋራ ያለው ግንኙነት በብሔራዊ ደህንነት ላይ የሚደቅነው አደጋ፣ የመድረኩ መታገድ 170 ሚሊዮን የሚሆኑ አሜሪካውያንን የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ይገድባል ከሚለው ስጋት ይበልጥ እንደሚያመዝን አስታውቋል። ቲክቶክ የግድ ለሌላ ወገን ተላልፎ መሸጡ የማይቀር ጉዳይ እንዳልሆነ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ ጠቁሟል።

በውሳኔው መሠረት አዲስ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን መጫን ወይም ማደስ አይችሉም። መተገበሪያው በስልካቸው ቢቆይም ሊሠራ እንደማይችል የፍትህ ሚኒስቴር ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ሰነድ ላይ ተመልክቷል።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰኞ ሥልጣኑን እስኪረከቡ ድረስ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እገዳውን እንዲያዘገይ ጠይቀው ነበር። ትረምፕ ቲክቶክን ከመታገድ እንደሚያድኑ ቢያስታውቁም፣ በምን መንገድ እንደሆነ አልገለጹም።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመጣው ትረምፕ ጉዳዩን በድርድር እንደሚፈቱ ባስታወቁበትና፣ የጆ ባይደን አስተዳደርም በመጨረሻው የሥልጣን ቀኑ ሕጉን ተፈፃሚ እንደማያደርግ ባመለከተበት ሁኔታ ነው።

ቲክቶክ ላይ 14.7 ሚሊዮን ተከታይ ያላቸውና የመድረኩን ጠቀሜታ የሚገነዘቡት ትረምፕ፣ የቲክቶክ ባለቤቶች እስከ አሁን ገዢ እንዳላገኙ ማስታወቃቸውን ከማይቀበሉት ከፍተኛ የሪፐብሊካን ፓርቲ የሴኔታ ዓባላት በተቃራኒ ቆመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG