“ሁከት እና ብጥብጥ በማሥነሳት” ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው አርቲስት ዐማኑኤል ሀብታሙ እና በእርሱ መዝገብ ሥር ያሉ 17 ግለሰቦች በዋስ ተለቀዋል።
ታሳሪዎቹ፣ በ50 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲወጡ ከተፈቀደላቸው ከአምስት ቀናት በኋላ መለቀቃቸውን፣ ጠበቃቸው አያሌው ቢታኔ ተናግረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢሕአፓን ሊቀ መንበር ዝናቡ አበራን ጨምሮ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ዐውድ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲፈቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንዲጸና፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማዘዙን ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
ኾኖም ታሳሪዎቹ እስከ አመሻሽ ድረስ እንዳልተለቀቁ፣ የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበሩ መጋቤ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም