ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሜሪካ የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ማመልክቻቸው በኢምግሬሽን ባለሥልጣናት ውድቅ የተደረገባቸው "ይግባኝ የማለት ሕገመንግሥታዊ መብት የላቸውም" ሲል ወስኗል፡፡
ሰኔ 18/2012 ዓ.ም. የተላለፈው ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ብዙዎቹን ጥገኝነት ጠያቂዎች ከሃገር ማባረር ለሚፈልገው የአሁኑ አስተዳደር ድርጊቱን እንዲገፋበት የሚያበረታታው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።