በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካንሳስ ሲቲው ግድያ ሁለት ሰዎች ተከሰሱ


የሱፐር ቦውል ዋንጫ አሸናፊ የሆነውን የከተማዋን ቡድን ቺፍስ ለመቀበል በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ባደረጉት ሰልፍ ላይ በተከፈተው ተኩስ አንድ ሰው ሲገደል፣ ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 22 ሰዎች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት አስታወቀዋል ካንሳስ ሲቲ፣ ሚዙሪ ክፍለ ግዛት
የሱፐር ቦውል ዋንጫ አሸናፊ የሆነውን የከተማዋን ቡድን ቺፍስ ለመቀበል በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ባደረጉት ሰልፍ ላይ በተከፈተው ተኩስ አንድ ሰው ሲገደል፣ ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 22 ሰዎች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት አስታወቀዋል ካንሳስ ሲቲ፣ ሚዙሪ ክፍለ ግዛት

ዩናይትድ ስቴትስ ሚዙሪ ክፍለ ግዛት ካንሳስ ሲቲ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ተኩስ ከፍተው አንድ ሰው በመግደልና 22 ሰዎችን በማቁሰል ሁለት ሰዎች ተከሰሱ፡፡ ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው አንድ ሚሊዮን ዶላር ዋስትና የተጠየቀባቸው መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቋል፡፡

ዶሚኒክ ሚለር እና ሊንደል ሜይስ የተባሉት ሁለቱ የአካባቢው ነዋሪዎች የተከሰሱት በአሜሪካ “ፉት ቦል” ስፖርት የሱፐር ቦውል ዋንጫ አሸናፊ የሆነውን የከተማዋን ቡድን ቺፍስ ለመቀበል በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ባደረጉት ሰልፍ ላይ፣ ነዋሪዎችን በማሸበር ፈጽመዋል በተባለው ግድያ፣ በትጥቅ በተፈጸመ ወንጀል እና የጦር መሣሪያን በሕገ ወጥ መንገድ በመጠቀም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

አቃቤ ህግ ሜይስ የተባለው አንደኛው ተከሳሽ ተኩሱን የከፈተው ከዚህ ቀደም ፍጹም ከማያውቀው ሰው ጋር ከተፈጠረ አተካራ በኋላ መሆኑን እና ንትርኩም ሽጉጥ ወደ መማዘዝ ማምራቱን አስታውቀዋል፡፡

ሜይ ሽጉጡን ቀድሞ በፍጥነት በመምዘዙ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችም ወዲያኑ ሽጉጦቻቸውን በመምዘዛቸው ተኩስ መከፈቱን አቃቢ ህጓ ገልጸዋል፡፡

ከመካከላቸው አንዱ ሁለተኛው ተከሳሽ ሚለር መሆኑን ጂን ፒተርስ ቤከር የተባሉ የጃክሰን ወረዳ አቃቤ ህግ ተናግረዋል፡፡

በከተማው ታዋቂ የሆነው የኬ ኬ ኤፍ አይ(KKFI) ሬዲዮ ጣቢያ ሙዚቃ አጫዋች (ዲጄ) ሊሳ ሎፔዝን የገደለው ጥይት የተተኮሰው ከሚለር ሽጉጥ መሆኑን አቃቢ ህጓ ተናግረዋል፡፡

ሜይስ እና ሚለር በተመሰረተባቸው የግድያ ወንጀል የእድሜ ልክ እስራት ሊፈረድባቸው እንደሚችል አቃቤ ሕጉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ከሁለቱ ተከሳሾች በፊት ሁለት ታዳጊ ወጣቶች መታሰራቸው ባለፈው ሳምንት መገለጹ ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG