ዋሺንግተን ዲሲ —
ቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋችና የፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ወዳጅ መሆኑ የሚነገርለት ዴኒስ ሮድማን፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን መገናኘታቸው እንዳስደሰተው ተናገረ።
ሮድማን ከሲኤንኤን ቴሌቪዥን ጋር ባካሄደው ቃለ ምልልስ፣ ሁለቱ ሀገሮች ሥምምነት ላይ እንዲደርሱ ያለውን ፍላጎት ገልፆ፣ “ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ይፋ በሆነ መንገድ ይህን በማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል” ብሏል።
ሮድማን ወደ ሰሜን ኮሪያ አምስት ጊዜ መመላለሱን አመልክቶ፣ ከዚያ ሲመለስ ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ እንደደረሰበት የገለፀው በልቅሶ መሆኑም ተመልክቷል።
ባለፈው ሰኞ ሲንጋፖር የደረሰው የሃምሳ ሰባት ዓመቱ የቅርጫት ኳስ ኮከብ፣ “ሰላም ከሲንጋፖር ይጀምራል” የሚል ካኒትራ ለብሶም ታይቷል።
ሮድማን አምስት ጊዜ የብሔራዊ ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና መሆኑም ይታወቃል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ