ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የአፋር መንፈሳዊ መሪ ሱልጣን ዐሊ ሚራሕ ሀምፍሬ በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ላይ ጽኑ አምነት እንደነበራቸው ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል። ኤርትራ በተገነጠለችበት ህዝባዊ ውሳኔ ወቅትም የአሰብ ጉዳይ ለብቻው በአፋር ህዝብ እንዲወሰንና ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት እንድትሆን ፍላጎታቸው ነበር ብለዋል ቤተሰቦቻቸው።
ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው ሀዘን ላይ የተቀመጡትን ዘመዶቻቸው አነጋግሮ የላከው ዘገብ ቀጥሎ ይቀርባል።