በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ አጥፍቶ፣ ጠፊው ፍንዳታ አደረሰ


ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ
ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ

ሶማሊያ ውስጥ በዋና ከተማው ሞቃዲሾ በስተምዕራብ በሚገኘ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ውስጥ ትናንት እሁድ በደረሰ የአጥፍቶ መጥፋት የቦምብ ፍንዳታ አንድ ወታደር ሲሞት ሌሎች ስድስት ደግሞ መቁሰላቸው ተነገረ፡፡

ለፍንዳታው ከአልቃይዳ ቡድን ጋር የተባበረው አልሻባብ ኃላፊነቱን መውሰዱን የሮይተር ዘገባ አመልክቷል፡፡

አጥፍቶ፣ ጠፊው ራሱን ከሌሎች ወታደሮች ጋር በማመሳሰል እሁድ ማለዳው ላይ ወደ ወታደራዊ ካምፑ የዘለቀ መሆኑን በጦር ሰፈሩ የነበረውን አንድ ወታደር ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፤

አልሸባብ ግን ባወጣው መግለጫ በወታደራዊ ጦር ሰፈሩ የነበሩ “32 ከሃዲ ወታደሮችን” ሲገድል ከ40 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ማቁሰሉን ገልጿል፡፡

መሰረታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉት አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ዛሬ ለቪኦኤ እንደተናገሩት አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚያደርሳቸው ጥቃቶች እስካሁን ረብ ያለው ድርጅት መሆኑን ለማሳወቅ ነው ብለዋል፡፡

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ባላፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር መንግሥታቸው ሽብርተኝነትን ከሶማሊያ እንደሚያስወገዱ ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG