በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ፖሊሶች ተገደሉ


አፍጋኒስታን ደቡባዊዋ ካንዳሃር ክፍለ ሀገር ውስጥ ውስጥ ዛሬ ዓርብ ማለዳ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ ሥድስት ፖሊሶች ገድሎ አሥር ሌሎች ማቁሰሉን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ገለፁ።

አፍጋኒስታን ደቡባዊዋ ካንዳሃር ክፍለ ሀገር ውስጥ ውስጥ ዛሬ ዓርብ ማለዳ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ ሥድስት ፖሊሶች ገድሎ አሥር ሌሎች ማቁሰሉን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ገለፁ።

አጥፍቶ ጠፊው ፈንጂ ባጨቀበት ወታደራዊ ተሽከርካሪ መኪና ማይዋንድ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ገብቶ ጥቃቱን ማድረሱን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል። ታሊባን ወዲያውኑ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ

የዛሬው ጥቃት የደረሰው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ አስቀድሞ ይፋ ያልሆነ ጉብኝት አድርገው ባግራም የአየር ኃይል ጦር ሠፈር ላይ ለአሜሪካውያን ወታደሮች ንግግር አድርገው ካመሰገኑዋቸው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መሆኑ ነው።

ፕሬዚደንት ትረምፕ በነሃሴ ወር ይፋ ያደረጉት አዲሱ የአፍጋኒስታን ስትራተጂ ሃገሪቱ ላይ ርምጃ እያስመዘገበ ነው ሲሉ ምክትል ፕሬዚደንቱ አስገንዝበዋል።

ምክትል ፕሬዚደንቱ ቀደም ብለው ከአፍጋኒስታን ፕሬዚደንት አሽራፍ አልጋኒ እና ዋና የመንግሥቱ ሥራ አስፈፃሚ አብዱላ አብዱላ ጋር ተገናኝተው ስለዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታን ስትራተጂና ስለሁለቱ ሀገሮች ትብብር ተወይይተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG